https://link.space/@tok99toto ladangtoto link alternatif k86toto login https://thewatchmakerproject.com/ pragmatic play https://mannawasalwa.ac.id/3/ladang-toto/ https://mannawasalwa.ac.id/3/s-mania/ https://bintangara.tabalongkab.go.id/public/klik88/ https://klik88.bintangara.tabalongkab.go.id/ https://ladangtoto.sakt1.co.id/ https://manyao.djmusicvibration.com.in/ https://ww.pn-jayapura.go.id/ ladangtoto https://fa.unjani.ac.id/wp-content/pg/ slot thailand mahjong login k86sport tok99toto login https://slot-toto.pa-sungailiat.go.id/ https://cokang.pa-blambanganumpu.go.id/ ladangtoto login http://103.3.46.79/funmania/ http://103.101.52.68:8005/kaizen88/ https://link-fun77toto.threeways.id/ https://bandar-fun77toto.diansigmaglobal.id/ https://ptbm.co.id/k86toto/ https://sisfo.diskominfo.pa-malangkota.go.id/ https://ftp.fhunwiku.ac.id/ https://103.181.182.174/ https://www.forex.ntu.edu.tw/tok99/ http://nkquoc.ntt.edu.vn/ https://pti.ubhi.ac.id/assets/777/ https://kgaswe.ac.bw/adm-pulsa/ https://szeus.bintangara.tabalongkab.go.id/ https://ptbm.co.id/togel-hongkong/ https://sdnbeneryk.sch.id/s-88/ https://pta-bali.go.id/img/s-macau/ https://pta-bali.go.id/img/s-x500/ https://pta-bali.go.id/img/angka-jitu/ https://sdnbeneryk.sch.id/s-5k/ https://pta-bali.go.id/img/s-jepang/ http://103.3.46.79/888slot/ https://inspektorat.bondowosokab.go.id/assets/s-thailand/ https://pta-bali.go.id/img/s-taiwan/ https://fun77.bintangara.tabalongkab.go.id/ https://yppdb.or.id/s-macau/ http://103.3.46.79/dana-fun77/ https://yppdb.or.id/pg-soft/ https://galvindo.co.id/fun77toto/ http://103.3.46.79/padma188/ http://103.3.46.79/gateszeus/ https://pa-sukabumi.go.id/img/fun77toto/ https://yppdb.or.id/ladang-toto/ https://pa-blambanganumpu.go.id/img/s-mahjong/ https://yppdb.or.id/ying77/ http://103.3.46.79/slot777/ http://103.3.46.79/slot88/ http://103.3.46.79/slot77/ http://103.3.46.79/dewatoto/ http://103.3.46.79/dewaslot/ https://pa-blambanganumpu.go.id/img/s-dana/ https://pa-blambanganumpu.go.id/img/s-jp/ http://103.3.46.79/hokifun/ http://103.3.46.79/gopayfun/ http://103.3.46.79/danafun/ https://yppdb.or.id/data-sydney/ https://smartech.co.id/fun77toto/ http://161.97.112.139/ https://yppdb.or.id/axiebet/ https://yppdb.or.id/s-bri/ https://yppdb.or.id/s-toto/ https://yppdb.or.id/s-jepang/ https://pa-blambanganumpu.go.id/img/joker-123/ https://yppdb.or.id/ladang-duit/ slot thailand http://103.3.46.79/rumah258/ http://103.3.46.79/megaforwin/ http://103.3.46.79/asia188/ http://103.3.46.79/66kbet/ http://103.3.46.79/gb777/ http://103.3.46.79/gudangtoto/ https://slot-pragmatic.pa-sawahlunto.go.id/ https://lintas-unitama.co.id/fun77toto/ https://synergylab.co.id/s-qris/ https://synergylab.co.id/s-ovo/ https://synergylab.co.id/s-gopay/ https://synergylab.co.id/s-linkaja/ https://synergylab.co.id/s-dubai/ https://disporapar.metrokota.go.id/ladangfunloh/ https://disporapar.metrokota.go.id/ladangfun77loh/ https://disporapar.metrokota.go.id/fun77linkaja/ | ርዕሶች | የሃይማኖት መግለጫ | የአላህ ስሞችና ባሕሪያት

ዉዱእ

7179

      ዉዱእ ትርጓሜ

የዉዱእ ቋንቋዊ ትርጉም

ውበትና ንጽሕና

የዉዱእ ሸሪዓዊ ትርጉም

ንጽሕና አግኝቶ ለመጥራራት ለተወሰኑ የአካል ክፍሎች ውሃን መጠቀም ነው፡፡

    ዉዱእን የሚመለከት ብያኔ (ሑክም)

    ዉዱእ ወይ ዋጅብ (ግዴታ) ነው፣ ወይም የተወደደ (ሙስተሐብ) ነው፡

    ሀ- ዉዱእ በሦስት ነገሮች ምክንያት ግዴታ ይሆናል

    1 - ሶላት፡-

    አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ ጊዜ (ለመቆም ባሰባችሁ ጊዜ) ፊቶቻችሁን እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) እበሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች ድረስ እጠቡ፡፡ . . ›› [አል-ማኢዳህ፡6]

    ዉዱእ ለሶላት

    2 - ከዕባን ለመዞር (ጠዋፍ ለማድረግ) ፡-

    ነቢዩ ﷺ የወር አበባ ላለባት ሴት ፡- ‹‹እስኪትጠሪ ጠዋፍ አታድርጊ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡

    ዉዱእ ለጠዋፍ

    3 - የቁርኣን መጽሐፍን (ሙስሐፍ) መንካት ፡-

    አላህ እንዲህ ብሏልና ፡- ‹‹የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡›› [አል-ዋቂዓህ፡79]

    ዉዱእ የቁርኣን መጽሐፍ (ሙስሐፍ) ለመንካት

    ለ - ከዚህ ውጭ ለሆኑት ዉዱእ የተወደደ ይሆናል፡፡

    ነቢዩ ﷺ ‹‹ሙእምን የሆነ ሰው እንጅ ሌላው በዉዱእ ላይ አዘውትሮ አይጠባበቅም፡፡›› [በአሕመድ የተዘገበ] ብለዋል፡፡ ተወዳጅነቱ ዉዱእ ለየሶላቱ ማደስ፣ለአላህ ዝክርና ለዱዓእ፣ቁርኣን በሚቀራበት ጊዜ፣ከእንቅልፍ በፊት፣ከገላ ትጥበት (ጉስል) በፊት፣ አስከሬን ለተሸከመ ሰውና ሶላት ባይደርስ እንኳ ዉዱእ በፈረሰ ጊዜ ሲሆን የዉዱእ ተወዳጅነት የተረጋገጠ (ሙአክከድ) ይሆናል፡፡

    ዉዱእ አላህን ለማወደስ (ለዝክር)
    ዉዱእ በእንቅልፍ ጊዜ
    ዉዱእ ቁርኣን በሚቀራበት ጊዜ
    ውዱእ አስከሬን ከተሸከሙ በኋላ

    የዉዱእ ትሩፋቶች

    1 - ለአላህ ውዴታ ምክንያት መሆኑ፡-

    አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹አላህ (ከኃጢአት) ተመላሾችን ይወዳል፤ተጥራሪዎችንም ይወዳል፣በላቸው፡፡›› [አል-በቀራህ፡6]

    2 - በቅያማ ቀን ኡመታቸው ፊቶቻቸው፣እጆቻቸውና እግሮቻቸው በዉዱእ ምክንያት የሚያበሩ ሆነው ስለሚመጡ፤ለሙሐመድ ﷺ ኡመት መለያ ምልክት መሆኑ፡፡

    ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ኡመቴ (ሕዝቦቼ) በትንሳኤ (ቅያማ) ቀን በዉዱእ ጊዜ የሚታጠቧቸው የውዱእ አካሎቻቸው (ፊቶቻቸው፣እጆቻቸውና እግሮቻቸው) የሚያበሩ፣ቦቃና አሻል (ጉርረን ሙሐጅጀሊን) [ጉርር ፡- የፈረስ ግንባር ላይ ያለው ነጭ ቦቃ ሲሆን፣ሙሐጅጀል ደግሞ በፈረስ አራት እግሮች ንጣት (አሻል) ነው፡፡ በሐዲሱ ማለት የተፈለገው በቅያማ ቀን በዉዱእ አካላት ላይ የሚታየው ብርሃን (ኑር) ነው፡፡] ሆነው ይመጣሉና ከመካከላችሁ ብርሃኑን (ቦቃና አሻሉን) የበለጠ ማራዘም የቻለ ሰው ያድርግ፡፡›› [በቡኻሪና በሙስሊም የተዘገበ]

    3 - ኃጢአትንና ጥፋቶችን ሚያብስ መሆኑ፡-

    ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ዉዱእ አድርጎ ዉዱኡን ያሳመረ ሰው፣ኃጢአቶቹ ከጥፍሮቹ ሥር ሳይቀር ከአካሉ ሙልጭ ብሎ ይወጣል፡፡›› [በሙሲሊም የተዘገበ]

    4 - ደረጃዎችን ከፍ ማድረጉ፡-

    ነቢዩﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አላህ ኃጢቶችን የሚያብስበትንና ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር ላመላክታችሁን? ሲሉ (ሰሓባ) ‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አዎ ይንገሩን› አሉና ነቢዩ ﷺ (በብርድና በመሳሰለው) እየከበደ [ምቹ ያልሆነውንና ሰው የማይወደው አስቸጋሪ ሁኔታ፡፡] ዉዱእ አሟልቶ ማድረግ፣ወደ መስጊዶች እርምጃዎችን ማብዛት፣ከአንዱ ሶላት በኋላ ተከታዩን ሶላት መጠባበቅ ነው፡፡ ይህ ነው በአላህ መንገድ ለመታገል መሰለፍ (ሪባጥ) ማለት፤ይህ ነው በአላህ መንገድ ለመታገል መሰለፍ (ሪባጥ) ማለት፡፡›› [በሙሲሊም የተዘገበ]

    የዉዱእ አደራረግ

    1 - ዉዱእ ለማድረግ ቁርጠኛ ውሳኔ (ንይ’ያህ) በልብ ማድረግ፡፡

    2 - ‹‹ብስምል’ላህ›› ማለት፡፡

    3 - መዳፎችን መታጠብ (ሦስት ጊዜ)፡፡

    4 - በመጉመጥመጥ ጊዜ ጥርስን መፋቅ (ተሰው’ዉክ)፡፡

    5 - አፍን መጉመጥመጥ፣በአፍንጫ ውሃ ስቦ ማስወጣት (ሦስት)፡፡

    - መጉመጥመጥ (መድመዷ) ውሃ ወደ አፍ አስገብቶ ማንቀሳቀስ ነው፡፡

    - ውሃ በአፍንጫ መሳብ (እስትንሻቅ) ውሃን በአፍንጫ ቀዳዳዎች በኩል በትንፋሽ ወደ ውስጥ መሳብ ነው፡፡

    - መድመዷና እስትንሻቅ የሚደረገው በአንድ ዝግን ነው፡፡

    - እስትንሣር ወደ ውስጥ የተሳበውን ውሃ ከአፍንጫ ማስወጣት ነው፡፡

    6 - ፊትን ጺምን አክኮ ከማፍተልተል ጋር (ሦስት ጊዜ) መታጠብ፡፡

    የፊት ወሰን በቁመት ከራስ ጸጉር መብቀያ እስከ አገጭ ወደታች፣ ወደ ጎን ከጆሮ እስከ ጆሮ ነው፡፡

    7 - የቀኝ አጅን ከጣቶች ጫፍ እስከ ክርን ድረስ ሦስት ጊዜ ማጠብ፣የግራውንም በዚህ ሁኔታ ማጠብ፡፡

    8 - ራስን ማበስ፡- በውሃ በራሰ እጅ ከፊት ራስ ወደ ኋላ እስከ ማጅራት ከዚያም እንደገና ወደ ፊት በመመለስ በማበስ (አንድ ጊዜ) ይከናወናል፡፡

    9 - በሁለቱ አመልካች ጣቶች መሀል ጆሮን፣ በአውራ ጣቶች ደግሞ የወጭውን ጆሮ (አንድ ጊዜ) ማበስ፡፡

    10 - የቀኝ እግርን እስከ ቁርጭምጭሚቶች ድረስ (ሦስት ጊዜ) ከዜያም የግራውን እግር በተመሳሳይ መልኩ ማጠብ፡፡

    11 - ዉዱእ ካበቁ በኋላ የሚከተለውን ዱዓእ ማድረግ፡- ‹‹አሽሀዱ አን ላእላሀ እል’ለል’ሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፤ወአሽሀዱ አን’ነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ፡፡›› [በሙሲሊም የተዘገበ]

    ትርጉሙ፡- ‹‹ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እርሱ አንድና ሸሪክ የሌለው መሆኑን እመሰክራለሁ፤ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛና አገልጋዩ መሆናቸውንም እመሰክራለሁ፡፡›› ማለት ነው፡፡ ‹‹አሏሁም’መ እጅዐልኒ ምነት’ተው’ዋቢን ወጅዐልኒ ምነል ሙተጠህሪን፡፡›› [በትርምዚ የተዘገበ]

    ትርጉሙ ፡-‹‹አላህ ሆይ! ከኃጢአት ተመላሽ ከሆኑት ሰዎች ጎራ አድርገኝ፤ከተጥራሪዎች (ራሳቸውን በብዛት ከሚያጸዱ) ሰዎች ጭፍራም አድርገኝ፡፡›› ማለት ነው፡፡ ‹‹ሱብሓነከ አሏሁምመ ወብሐምድከ ፤አሽሀዱ አን ላእላሀ እል’ላ አንተ፣አስተግፍሩከ ወአቱቡ እለይከ፡፡›› [በነሳኢ የተዘገበ]

    ትርጉሙ‹‹አላህ ሆይ! ጥራት ላንተ ተገባ፤ምስጋናም ላንተ ይሁን፤ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እመሰክራለሁ፤ምሕረትህንም እለምነሃለሁ፤ከኃጢኣቴ ተጸጽቼ ወደ አንተ እመለሳለሁ፡፡›› ማለት ነው፡፡

    መዳፎችን (ሦስት ጊዜ) መታጠብ
    መጉመጥመጥ (ሦስት ጊዜ)
    አስትንሻቅ (ሦስት ጊዜ)
    ወሃን ከአፍንጫ ማስወጣት (ሦስት ጊዜ)
    ፊትን መታጠብ (ሦስት ጊዜ)
    ጺምን ማፍተልተልና ወደ ሥሩ እንዲዳረስ ማድረግ
    ሁለት እጆችን ከጣቶች ጫፍ አንስቶ እስከ ክርን መታጠብ (ሦስት ጊዜ)
    ራስን ማበስ
    መሐል ጆሮን አንድ ጊዜ ማበስ
    ሁለት እግሮችን እስከ ቁርጭምጭሚቶች ድረስ (ሦስት ጊዜ)

    ለዉዱእ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች (ሹሩጥ)

    1 - ውሃዉ ንጹሕ (ጠሁር) መሆን፡፡

    2 - ውሃው ሕጋዊ መሆን፣ለምሳሌ የተሰረቀ አለመሆን፡፡

    3 - እንደ ቅባትና ቀለሞች የመሳሰሉ ዉሃ ወደ ቆዳ እንዳይደርስ የሚያደርጉ ነገሮችን ማስወገድ፡፡

    ቅባት ነክ ነገሮችን ማስወገድ

    የዉዱእ ግዴታዎች

    1 - ንይ’ያህ ፡- የሚደረገው በልብ ነው፤በአንደበት አይነገርም፡፡ ያለ ዉዱእ ንይ’ያህ ራሱን ለማቀዝቀዝ አስቦ፣ወይም ለንጽሕና ብሎ ለመታጠብ ዓላማ የዉዱእ ተግባሮችን መፈጸም ዉዱእ ተደርጎ አይቆጠርም፡፡

    2 - ፊትን መታጠብ፡- መጉመጥመጥና ውሃ በአፍንጫ ስቦ ማስወጣትም አብሮት የሚካተት ነው፡፡

    3 - ሁለት አጆችን እስከ ክርኖች ድረስ መታጠብ፡፡

    4 - ራስን በራሰ እጅ ሙሉ በሙሉ ማበስ፣ጆሮዎችም በዚህ ሥር ይጠቃለላሉ፡፡

    5 - ሁለት እግሮችን ከቁርጭምጭሚቶች ጭምር መታጠብ፡፡

    6 - ከላይ በተዘረዘረው መሰረት ቅደም ተከተሉን መጠበቅ፡፡

    የዉዱእ ሱንናዎች

    1 - በዉዱእ መጀመሪያ ላይ መዳፎችን ሦስት ጊዜ መታጠብ፡፡

    2 - ጥርስን መፋቅ (ሰዋክ መጠቀም)፡፡

    3 - ራስና ጆሮዎች ሲቀሩ የወዱእ አካላትን ሦስት ሦስት ጊዜ ማጠብ፣ራስና ጆሮ አንድ ጊዜ ብቻ ይታበሳሉ፡፡

    4 - በዉዱእ አካላት ትጥበት ቀኝን ማስቀደም፡፡

    5 - አሻልን (ጉርርን) ማራዘም፡- ማለትም ክርኖችና ቁርጭምጭሚቶች ሲታጠቡ ከወሰን አልፎ ጨምሮ መታጠብ፡፡

    6 - ወሃ ወደ ፊት ቆዳ እንዲደርስ ለማድረግ ጺምን በጣቶች በማፍተልተል አክኮ ወሃውን ለቆዳ ማድረስ፡፡

    7 - የአጅና ግር ጣቶችን በመዘርዘር ወሃ በመካከላቸው እንዲደርስ ማድረግ፡፡

    8 - አካላቱን አሽቶ ማጠብ፤ ዝም ብሎ ውሃ ላያቸው ላይ ማፍሰስ ብቻ በቂ አይደለም፡፡

    9 - ውሃን መቆጠብ፡፡ ነቢዩ ﷺ ‹‹በዚህ ኡመት ውስጥ በዉዱእ ረገድ ከተገቢው በላይ ወሰን የሚያልፉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡›› [በአቡ ዳውድ የተዘገበ]

    10 - ከዉዱእ በኋላ ዱዓእ ማድረግ፡፡ ነቢዩ ﷺ ‹‹ከናንተ መካከል ዉዱእ አድርጎ ዉዱኡንም ያሟላና ከዚያም ‹አሽሀዱ አን ላእላሀ እል’ለል’ሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፤ወአሽሀዱ አን’ነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ፡፡› ያለ፣ ስምንቱ የጀነት መግቢያ በር ተከፍተውለት በፈለገው (በር) የሚገባ ቢሆን እንጅ ማንም ሰው የለም፡፡›› [በትርምዚ የተዘገበ] ብለዋል፡፡

    11 - ከዉዱእ በኋላ ሁለት ረክዓ መስገድ፡፡ ነቢዩ ﷺ ‹‹እኔ አሁን እንዳደረግሁት ዓይነት ዉዱእ አድርጎ ነፍሱ ስለ ዓለማዊ ሕይወት ጉዳይ ምንም ሳትወሰውሰው ሁለት ረክዓ ሶላት ለሰገደ ሰው፣አላህ ያለፈ ኃጢአቱን ይምረዋል፡፡ [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡

    ሰዋክ መጠቀም
    ጣቶችን መዘርዘር
    አሻልን ማራዘም

    ዉዱእ የሚያፈርሱ ነገሮች

    1 - በሁለቱ መንገዶች [ሁለቱ መንገዶች የሽንትና የዓይነ ምደር ማውጫዎች ናቸው፡፡] ከሆድ ወደ ውጭ የወጡ እንደ ሽንት፣ ዓይነ ምድርና አየር ያሉ ነገሮች ሁሉ፡፡ ነቢዩ ﷺ ‹‹ዉዱኡን ካፈረሰ እንደገና ዉዱእ ካላደረገ በስተቀር አላህ ያንዳችሁን ሶላት አይቀበልም፡፡>> [በሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡

    2 - ሙሉ በሙሉ ራስን የሚያስት ከባድ እንቅልፍ፤ራስን መሳትና ሙሉ ማደንዘዣ መውሰድን የመሳሰሉ ነገሮችም በዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

    3 - የግመል ሥጋ መብላት፡፡ ከጃቢር ብን ሱመራ በተላለፈው መሰረት አንድ ሰውየ ነቢዩን ﷺ ‹‹የግመል ሥጋ ከበላን ዉዱእ እናደርጋለን ወይ? ብሎ ሲጠይቃቸው አዎ ፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]ማለታቸው ተዘግቧል፡

    4 - የወሲብ ብልትን ምንም ነገር በመካከል ሳይኖር በቀጥታ በእጅ መንካት፡፡ ቡስራ ብንት ሰፍዋን ባስተላለፉት መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ‹‹ብልቱን የነካ ሰው ዉዱእ ያድርግ፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] ሲሉ መስማታቸውን ተናግረዋል፡

    የግመል ሥጋ መብላት
    ጥልቅ እንቅልፍ

    ጠቃሚ ነጥቦች

    1 - አንድ ሙስሊም ከእንቅልፉ ተነስቶ ውሃ ከያዘ እቃ ውስጥ ዉዱእ ማድረግ ቢፈልግ መጀመሪያ እጆቹን ሦስት ጊዜ ሳይታጠብ ውሃውን በእጁ መዘገን የለበትም፡ ነቢዩን ﷺ ‹‹አንዳችሁ ከእንቅልፉ በሚነሳበት ጊዜ ሦስት ጊዜ እስኪያጥበው ድረስ እጁን (ውሃ በያዘ) እቃ ውስጥ አይክተት፤ አጁ ዬት እንዳደረ አያውቀውምና፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡

    2 - መታጠቡ ግዴታ ወደ ሆነ የዉዱእ አካል ሁሉ ውሃ እንዲደርስ ጥንቃቄ ማድረግ፤በተለይም በእጅና እግር ጣቶች መካከል በጆሮና ጺም መካከል ባለው ቦታ፣ወደ ሁለቱ ክርኖች፣ሁለቱ ቁርጭምጭሚቶችና ሁለቱ ተረከዞች በደንብ እዲዳረስ ማድረግ፡፡ ነቢዩን ﷺ ‹‹ለተረከዞች ከእሳት (ቅጣት) ወየውላቸው፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] ብለዋልና፡፡

    3 - መርሁ በተረጋገጠው ነገር ላይ መሞርከዝ ነው፡፡ አንድ ሰው በእርግጠኝነት ዉዱእ እንዳለው የሚያውቅ ሆኖ ወዱኡ ፈርሷል አልፈረሰም የሚል ጥርጣሬ ካደረበት ዉዱኡ አለ በሚለው የተረጋገጠ (የቂን) ነገር ላይ ይሞረኮዛል፡፡

    ዉዱእ እንደ ሌለው በእርግጠኝነት የሚያውቅ ሆኖ እያለ ወዱኡ አድርጌያለሁ አላደረኩም የሚል ጥርጣሬ ካደረበት እርግጠኛው ነገር (የቂኑ) ዉዱእ የሌለው መሆኑ ነው፡፡

    4 - አንድ ሙስሊም ወዱእ አድርጎ የዉዱእ አካላትን አንዳንድ ጊዜ ወይም ሁለት ሁለት ጊዜ፣ወይም ከፊሉን አንድ ጊዜ፣ ከፊሉን ሁለት ጊዜ፣ከፊሉን ደግሞ ሦስት ጊዜ ታጥቦ ከሆነ ዉዱኡ ትክክለኛ ሲሆን በላጩን ነገር የተወ ይሆናል፡፡

    5 - በመርሳት ያለ ዉዱእ የሰገደ ሰው እንዳስታወሰ ሶላቱን እንደገና መስገድ ይኖርበታል፡፡

    6 - ዉዱእ ካደረገ በኋላ ነጃሳ ነገር ከነካው ነጃሳውን ብቻ ማስወገድ እንጂ ዉዱእ ማድረግ አያስፈልገውም፡፡ ይህ ነጃሳ እንጂ ሐደሥ አይደለምና፡፡

    በጆሮና ጺም መካከል ያለው ቦታ
    ከእንቅልፍ ከተነሱ በኋላ እጅን እቃ ውስጥ መክተት
    የሁለቱ እግሮችን ጣቶች መዘርዘር
    የውስጥ ተረከዝ
    ዉዱእና አጠቃላይ ጤና
    የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚያሳትመው ሶርስ በተሰኘው መጽሔት ላይ የሚከተለውን እናገኛለን፡- ‹‹በእስላማዊ ማህበረሰቦች ዘንድ ያለው ቀጣይነት ያለው ትጥበትና ለሶላት የሚደረገው ዉዱእ፣በሦስተኛው ዓለም አገሮች ውስጥ ለዐይነ ስውርነት የመጀመሪያው መንስኤ ሆኖ የሚቆጠረውን የትራኮማ በሽታን ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ አግዟል፡፡ በበሽታው የተያዙ ወደ 500 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በዓለም አገሮች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከሶላት በፊት በያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ገዴታ የሆነውን እስላማዊ የንጽሕና አጠባበቅ መንገድ ዓይነ ስውርነትን መከላከል ይችላሉ፡፡ ለንጽሕና ሥርዓቱ ተገዥ በሆኑ ሕብረተሰቦች መካከል በዚህ በሽታ የመያዙ ዕድል እጅግ አነስተኛ መሆን ብቻ ሳይሆን ጭራሽም እስከ አለመኖር ደረጃ መድረሱ ተስተውሏል፡፡ [ግያሥ አሕመድ፣አጥጢብ አንነወዊይ ፊደውእል ዕልም]

    ተገቢ አይደለም

    1 - ለዉዱእ በአንደበት ንይያህ ማድረግ፡፡

    2 - ውሃን ማባከን፡፡

    3 - ትጥበቶችን ከሦስት ጊዜ በላይ መጨመር፡፡ ይህም አንድ ገጠሬ ዐረብ ስለ ዉዱእ ሊጠይቃቸው ወደ ነቢዩ መጥቶ ነቢዩ ሦስት ሦስት ጊዜ በማድረግ ዉዱእ አደራረግን ካሳዩት በኋላ ‹‹ዉዱእ እደዚህ ነው፣በዚህ ላይ የጨመረ ሰው በእርግጥ አጥፍቷል፤ወሰን አልፏል፤ተጋፍቷል፡፡›› [በአቡ ዳውድ የተዘገበ] ባሉት መሰረት ነው፡፡

    አካሉ በሦስት ትጥበቶች ካልጸዳ ግን፣ለምሳሌ ቀለም ወይም ሌላ ቶሎ የማይለቅ ነገር የነካው ሰው ከሦስት ጊዜ በላይ ማጠብ ይፈቀዳል፡፡

    4 - ዉዱእን በሚገባ አሟልቶ አለማድረግ ፡- አንድ ሰው ዉዱእ አድርጎ እግሩ ላይ አንዱን ጥፍር ውሃ ሳያስነካ መቅረቱን ነቢዩ ﷺ አይተውት ፡- ‹‹ተመልስህ ዉዱእህን አሳምረው፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] አሉትና ተመልሶ ከዚያ በኋላ መስገዱ ተዘግቧል፡፡

    ዉዱእ ባለማሳመር ውስጥ የሚከተሉት ይካተታሉ፡-

    ሀ- ሁለቱን ቁርጭምጭሚቶች አለማጠብ፡፡

    ለ- ሁሌን ክርኖች አለማጠብ፡፡

    ሐ- በጆሮና በጺም ጸጉር መካከል ያለውን ቦታ አለማጠብ፡፡

    መ- የግራ እጅ መዳፍን ከግራ እጅ ጋር አለማጠን፡፡

    ሰ- ቀለም እያለበት ዉዱእ የሚደርግ ሰው፡፡

    ረ- በጣቶቿ ላይ ውሃ ወደ ቆዳዋ እንዳይደርስ የሚያግድ ጌጥ (ሜክ አፕ) እያለባት ዉዱእ ያደረገች ሴት፡፡

    ሠ- ውሃ በመካከላቸው ሳይገባ በሚቀርበት ጊዜ የእግር ጣቶችን አለመዘርዘር፡፡

    5 - አንገትን ማበስ ፡-

    ከዉዱእ በፊት ወይም ዉዱእ ከተሟላ በኋላ አንገትን ማበስ ስላስፈለገው ብቻ አድርጎት ካልሆነ በስተቀር ይህ በምንም ነገር ከዉዱእ ጋር አይገናኝም፡፡

    6 - በሸሪዓው ያልተደነገገ ዝክር ማድረግ፣ለምሳሌ፡-

    - እያንዳንዱን አካል ሲታጠቡ ለየአካሉ የተለየ ዱዓእ ማድረግ፡፡

    - ዉዱእ ላደረገ ሰው ‹‹ዘምዘም›› ማለት፡፡

    7 - በመወስወስ በሽታ የተያዘ ሰው ዉዱእ ደጋግሞ ማድረግ፡፡ ይህ ሰይጣን ሲጫወትበት ዉዱእህ ተበላሽቷል፣ወይም አልተሟለም እያለ ዕባዳን እዲሰላች ሲወሰውሰው ከሚገባው በላይ ተጨንቆ እስትንጃእ አንዲያደርግ ወይም አንዱን የዉዱእ አካል ከታዘዘው በላይ ደጋግሞ እዲያጥብ ይገፋፈዋል፡፡

    ውሃን ማባከን


Tags: