በሶላት ውስጥ የተፈቀዱ የተጠሉና ሶላትን የሚያበላሹ ነገሮች

5764

    አንደኛ - በሶላት ውስጥ የሚፈቀዱ ነገሮች

    1 - ከቅብላ ፊትን ካለማዞር ግዴታ ጋር የሆነ ችግር ሲያጋጥም በቅብላ በኩል ያለውን በር መክፈትን ለመሳሰለ ነገር መራመድ፡፡

    2 - ሶላት ውስጥ ሕጻናትን መሸከም፡፡

    3 - ሶላት ውስጥ እባብና ጊንጥን መግደል፡፡

    4 - የሆነ ጉዳይ ሲያጋጥም አንገትን ማዞር፡፡

    5 - ሶላት ውስጥ ማልቀስ፡፡

    6 - ለወንዶች ‹‹ሰብሓነል’ሏህ›› ማለት፣ለሴቶች ማጨብጨብ፡፡

    7 - ኢማሙ ሲሳሳት ማረም፡፡

    8 - ሶላት ውስጥ ለሌለው ሰው ሰላምታ በእጅ ምልክት ምላሽ መስጠት (የመዳፍ የውስጥ ክፍል ወደ መሬት የውጭውን ክፍል ወደ ላይ በማድረግ)፡፡

    9 - የሆነ ጉዳይ ሲያጋጥም ግልጽና አስረጅ የሆነ ምልክት መስጠት፡፡

    10 - ይህን የሚጠይቅ ነገር ካየ አላህን ማመስገን፡፡

    11 - ሶላት ውስጥ ምራቅና አክታን በግራ በኩል መትፋት፡፡

    12 - ከሰጋጅ ፊት አቋርጦ የሚያልፍን ሰው ማገድ፡፡

    ሁለተኛ - በሶላት ውስጥ የሚጠሉ ነገሮች

    1 - በተበታተነ ሃሳብ፣ከራሱ ጋር ወይም ከፊት ለፊቱ ከሶላት የሚወሰውሰው ነገር እያለ ወደ ሶላት መግባት፡፡ በሽንት፣በዓይነ ምድር ወይም በአየር ሆዱ እየተወጠረ መስገድ፡፡ በጣም እየራበውና እየጠማው፣የሚያስጎምጅ ምግብ ቀርቦ እያለ ወይም ከሶላቱ ትኩረቱን የሚሻማ ነገር እየተመለከተ መስገድ፡፡

    2 - ትርጉም የለሽ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ማለትም ኹሹዕና እርጋታን የሚጻረር ሁኔታ ሶለት ውስጥ መፈጸም፡፡ ያለ ምክንያት መንቀሳቀስ፣ጺምን፣ልብስና የራስ መሸፈኛን፣የእጅ ሰዓትን መነካካት፤ጣቶችን ያዝ ለቀቅ ማድረግና ማቆላለፍን የመሳሰሉ ነገሮችን መፈጸም፡፡

    3 - ያለ ምክንያት ሶላት ውስጥ ፊትን ማዞር፡፡ ይህም ሙሉ በሙሉ አካልን ከቅብላ ካለማዞር ግዴታ ጋር ሲሆን፣ይህን ማድረግ ሶላት ያበለሻል፡፡

    4 - ሶላት ውስጥ ወገብን መያዝ፣ይህ የአይሁድ ሥራ ነው፡፡

    5 - ሶላት ውስጥ አፍና አፍንጫን መሸፈን፡፡

    6 - ልብስን እጅጌንና የመሳሰሉትን መሰብሰብና ማጠፍ፡፡

    7 - ለወንዶች ጸጉርን ሰብስቦ ወደ ኋላ መጎንጎን፣በዚህም እጁን የፍጥኝ የታሰረ ይመስል ጸጉሩ አብሮት ሱጁድ እንዳይወርድ ያደርጋል፡፡

    8 - ወደ ቅብላ አቅጣጫ ወይም በስተቀኝ መትፋት፡፡

    9 - ወደ ሰማይ አንጋጦ ማየት፡፡

    10 - ያለ ምክንት ዓይኖችን መጨፈን፡፡

    11 - በሱጁድ ጊዜ ሁለቱን ክንዶች መሬት ላይ ማሳረፍ፡፡

    ሦስተኛ - ሶላትን የሚያበላሹ ነገሮች

    1 - ከሶላት ቅድመ ሁኔታዎች (ሸርጦች) ውስጥ አንዱን የሚጻረር፣ጦሃራን የሚያበላሽ ነገር መከሰትን፣ወይም ሆን ብሎ ሐፍረተ ገላ መግለጥን፣በሙሉ ሰውነት ከቅብላ መዞርንና ንይ’ያ ማቋረጥን የመሳሰለ ሁኔታ መፈጠር፡፡

    2 - ሆን ብሎ አንድን የሶላት ሩክን ወይም ዋጅብ መተው፡፡

    3 - ከሶላት ተግባራት ውጭ የሆነ መሄድና ብዙ እንቅስቃሴ ማድረግን የመሳሰለ ምክንያት የሌለው ብዙ ሥራ መስራት፡፡

    4 - መሳቅና መንሰቅሰቅ፡፡

    5 - ሆን ብሎ መናገር፡፡

    6 - ሆን ብሎ መብላትና መጠጣት፡፡

    7 - አንድ ረክዓ ወይም ማእዘን ሆን ብሎ መጨመር፡፡

    8 - ሆን ብሎ ከኢማሙ አስቀድሞ ሰላምታ ማለት፡፡